አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ማን ናቸው ?

ትውልድ እና እድገታቸው አዲስአበባ ከተማ ነው።የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስአበባ ከተማ በአድቬንቲስት ሚሽን እና በቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተምረዋል።

በመቀጠልም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ በውጭ ቋንቋዎች ጥናት ፣ከኮተቤ ዩኒቨርስቲ በስፖርት ሳይንስ ተመርቀዋል::

ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ በአትሌቲክስ አሰልጣኝነት ፣ከኮተቤ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት ማስተርስ ዲግሪያቸውን ይዘዋል።

በተጨማሪም ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ከህንድ አገር አንድህራ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ተመርቀዋል።

የካበተ የስራ አገልግሎታቸውንና ልምዳቸውን ስንመለከት:-

በረዳት ፕሮፌሰርነት በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ለስምንት አመታት አገልግለዋል፡፡

በአሰልጣኝነት ለሰባት አመታት ፣በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት እና በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ዳይሬክተርነት ለአምስት አመታት አገልግለዋል፡፡

የተለያዩ ከ20 በላይ የምርምር ጥናቶችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች ከማሳተም ባለፈ የኢትዮጵያ የስፖርት ሪፎርም፣ የስፖርት ፖሊሲ፣ የስፖርት ህግ እና የለውጥ ስትራቴጂክ እቅዶች በጥናት መነሻነት አዘጋጅተዋል፡፡

የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የስፖርት ሳይንስ ጆርናል በሀገር ውስጥ በትምህርት ሚኒስቴር እና በአፍሪካ( Online Journal System) እውቅና እንዲያገኝ በማድረግ በዋና ኤዲተር( Editor In Chief) ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከ200 በላይ በዩኒቨርሲቲ እና በሙያ ማህበራት የተዘጋጁ የምርምር ጆርናሎች ኤዲቶሪያል ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአሰልጣኞች የሙያ ብቃት ከፍተኛ መዛኝ ናቸው፡፡

መልካም የስራ ዘመን !

Categories: Uncategorized