ከአትሌቲክስ ባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይት ተደረገ።
መስከረም 22/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአትሌቲክስ ባለድርሻ አካላት ጋር በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዝግጅትና አፈፃፀም በተመለከተ በካፒታል ሆቴል ውጤታማ ውይይት አካሂዷል ።
መንግስት ስፖርቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ ገልፀዋል ።
።
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ሚኒስትር ዲኤታው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አሁን የተጀመሩ ሪፎርሞችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ እና መንግስት ለዚህ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን “ፌዴሽኑ ካሁን በኃላ አሰራር እና መመሪያዎች በተገቢው መልኩ በመተግበር” ችግሮችን ለመቅረፍ ይሰራል ብለዋል።
አሁን ካለንበት ችግር በፍጥነት ካልወጣን አትሌቲክሱ አደጋ ላይ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ባለድርሻ አካላት በጋራ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተካፈሉት ባለሙያዎች ጥያቄያቸውን አቅርበው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣
የክልልና ከተማ አስተዳድሮች ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ፤ የክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች ፤ አሰልጣኞች ፤የሙያ ማህበራት፣ አትሌቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።