በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የመጀመሪያው ተጓዥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ቶኪዮ ደርሷል ።

ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም

በጃፓን ቶኪዮ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የመጀመሪያው ልዑክ ቡድን በሰላም ጃፓን ቶኪዮ ደርሰዋል ።

ልዑክ ቡዱኑ ናሬታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በጃፓን የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

ሻምፒዮናው የፊታችን ቅዳሜ የሚጀመር ይሆናል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በርምጃ እና ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ ርቀቶች በሁለቱም ፆታ ትሳተፋለች።

Loading

Categories: Uncategorized