በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ምሽት 4:35 ወደ ጃፓን ቶኪዮ አቅንቷል ።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከ800 ሜትር ጀምሮ እስከ ማራቶን እና ርምጃን ጨምሮ ባሉት ርቀቶች የምትሳተፍ ሲሆን ዛሬ 39 አባላትን ያካተተ ልዑክ ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋይ
ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስልጠና ጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት በላይነሽ ዋቅጂራ ፣የፌዴሬሽኑ ም/ጽቤት ሃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ እና የተሳትፎና ውድድር ንዑስ የስራ ሂደት መሪ ተወካይ አቶ ብስራት ለጥይበሉ
በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የልዑክ ቡድኑን ሸኝተዋል ።
መልካም ጉዞ !
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !