የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።
ከሌጎስ በስተ ሰሜን 130 ኪሎ ሜትር የምትርቅ በናይጄሪያ ደቡብ ምዕራብ ክፍል በኦጉን ግዛት የምትገኘው የአበኩታ ከተማ የአፍሪካ ከ18 እና 20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ከጁላይ 16-20/2025 አስተናግዳ አጠናቃለች::
በዚህ ሻምፒዮና ላይ ከ44 ሀገራት የተወጣጡ 457 ሴት እና 563 ወንድ በድምሩ1,020 አትሌቶች የተፎካከሩበት ሲሆን ኢትዮጵያ 28 አትሌቶች በማሳተፍ በ2 ወርቅ፣ በ3 ብር እና በ5 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች።
በቀጣይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡና ስሟን የሚያስጠሩ ፤ አዳዲስ እና ተተኪ አትሌቶችን የተመለከትንበት ሻምፒዮና ሆኖ አልፏል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዕድሜ ተገቢነት ምርመራ ላይ የተሰራ ተግባር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንደ ተሞክሮ ሁኖ የታየበት ሻምፒዮና ነበር።
ልዑክ ቡድኑ ዛሬ ምሽት 3:00 አዲስአበባ ይደርሳል።
ልዑክ ቡድኑ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል።
ቡዱኑ በነገው ዕለትም ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም በቼክ ኢን ሆቴል የማበረታቻ የሽልማት እና እውቅና መድረክ ይደረግለታል ።
ውጤቱን በዝርዝር ስንመለከት :-
በ5,000ሜ ሴት እርምጃ ከ18 ዓመት በታች ህይወት አምባው
በ800ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች- ኤልሳቤጥ አማረ
በ3000 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች -ደስታ ታደለ
በ3000ሜ ሴት ከ20 ዓመት በታች -ትርሐስ ገብረሂወት
በ1500 ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች -ኤልሳቤጥ አማረ
በ1500 ሜ ሴት ከ18 ዓመት በታች – ደስታ ታደሰ
በ3000 ሜትር ሴቶች ከ18 ዓመት በታች ብርነሽ ደሴ
በ400ሜ ሴት ከ18 ዓመት -ባንቻአለም ቢክስ.
በ1500 ሜ ወንድ ከ18 ዓመት በታች – ሳሚኤል ገብረሃዋርያ
በ800ሜ ወንድ ከ20 ዓመት በታች ሲሳይ ዓለቤ