በፈረንሳይ ሊቪ የዓለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል

የካቲት 07/2017 ዓ.ም
በፈረንሳይ ሊቪ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር በሴቶች
✅ 800 ሜትር ፅጌ ድጉማ አሸንፋለች ።
አትሌት ፅጌ 1:59.02 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች ።


✅በሴቶች 3000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትሎ በመግባት አሸንፈዋል ።
አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ 8:19.98 በመግባት በአንደኝነት ስታሸንፍ ፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 8:25.12 እና ብርቄ ሀየሎም 8:25.37 በመግባት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
በተያያዘ አትሌት ብርቄ ሀየሎም ከ20 አመት በታች አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባለች ።

✅በወንዶች 3000 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
አትሌት ቢኒያም መሐሪ 7:29.99 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝና የግል ምርጥ ስዓቱን በማስመዝገብ እንዲሁም አትሌት ጌትነት ዋለ 7:31.39 በመግባት ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል

✅በሴቶች 1500 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትሎ በመግባት አሸንፈዋል ።
አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ3:58.89 በመግባት የዓመቱን ፈጣን ስዓት በማስመዝገብ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ፣አትሌት ሀብታም አለሙ በ4:03.86 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ እንዲሁም አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በ4:05.06 ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትሎ በመግባት ድል ተቀዳጅተዋል ።

Categories: Uncategorized, ዜና