የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና መስጠት ጀመረ።

##################################################

ጥር 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ ዳኝነት ስልጠና በአዲስአበባ ስፖርት ስልጠና ማዕከል ዛሬ ጥር 14/2017 ዓ.ም መስጠት ጀምረዋል ።

በስልጠናው መርሀግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ ይህንን የስልጠና እድል ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ በተደረገ ውይይት የተገኘ መሆኑን በማንሳት ፣ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን በመጠቆም ፣ፌዴሬሽኑ ለስልጠናው ውጤት እና ስኬታማነትም በቂ በጀት መመደቡን፣ በኢትዮጵያዊ ኢንስትራክተር ስልጠናው መሰጠቱ ለአገራችን ትልቅ ኩራት መሆኑን አስገንዝበዋል ።

ኃላፊው በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ በማሳሰብ፣ መልካም ምኞታቸውን ገልጿል ።

ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

ስልጠናው፣በኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው እስከ ጥር 18/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ።

Categories: Uncategorized