የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከትግራይ እና ከድሬዳዋ በመቀጠል በአማራ ክልል በደሴ ከተማ የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጠኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።
############################
ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም. ደሴ
ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ አቅዶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የህፃናት አትሌቲክስ ስልጠና ነው ። በዚህም መሰረት ወደ ደሴ ከተማ በማቅናት በከተማው ካሉት ሁለት ትምህርት ቤቶች ማለትም ከባህር ጠለል በላይ 2738 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው የቁርቁር አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከባህር ጠለል በላይ በ2628 ሜትር
ከፍታ ላይ የሚገኘው የቦሩ ሜዳ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምርህት ቤት የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጠኞች ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል ።
በዛሬው መርኃግብር ስልጠናውን የሚሰጡት ኢንስትራክተር አቶ አድማሱ ሳጂ የኢ.አ.ፌ. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣አቶ ጊዜ አድነው የኢ.አ.ፌ. የአትሌቲክስ ስልጠና ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ እና አቶ ብስራት ለጥይበሉ የኢ.አ.ፌ. የውድድርና ተሳትፎ ከፍተአኛ ባለሞያ ከከተማው የስፖርት ክፍል ሃላፊዎች ጋር በመሆን ከትምርትቤቶቹ ርዕ/መምህራን እና ሰልጣኝ መምህራን ጋር :-
ስለ ህፃናት አትሌቲክስ የግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የህፃናት አትሌቲክስ ለመስራት ምን ያስፈልጋል ፣ ፌዴሬሽኑ ስለሚያደርገው ድጋፍ ፣ እና በቀጣይ እንዴት ከፌዴሬሸኑ ጋር እንሰራለን በሚሉ ጉዳዮች ዙርያ ሰፊ ውይይት አካሄደዋል ።