የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ሽኝት ተደረገለት።

xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxc

ግንቦት 01/2018 ዓ.ም 

በጋና ዋና ከተማ አክራ በሚካሄደው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ትላንት  ምሽት ሽኝት ተደርጎለታል።

በሽኝት መረሐ ግብሩ የተገኙት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ መኪዩ መሐመድ ሀገርን መወከል ትልቅ ዕድል ነው ያሉ ሲሆን በመተባበር ፣ በመተጋገዝ ፣ በጋራ በመሆን እና አሰልጣኞች የሚሉትን በመስማት በዲስፒሊን የአገራችሁን ሰንደቅ አላማ ከፍ እድታደርጉ የአገራችሁን ስም እንድታስጠሩ ሲሉ ለልዑካን ቡድኑ አሳስበዋል።

ሌላኛው በሽኝት መረሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን :-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከመንግስት ጋር በጋራ ተቀራርቦ እየሰራ መሆንን በመግለጽ መግስት ለስፓርቱ ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየሰራ በመሆኑ በማመስገን አሁንም አጠናክሮ እዲቀጥል ጠይቀዋል አክለውም በመተባበር አብሮ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እደሚሰሩ ተናግረዋል ።

በመቀጥለም የቡድኑ አሰልጣኝ ንጉሴ ጌቻሞ (ዶር) “ለአንድ ሀገር ለአንድ ባንዲራ ታሪክ ለመስራት እንዋደቃለን ፣ በመካከላችን ምንም መከፋፈል ሳይኖር ወደ ስፍራው በማቅናት በውድድሩም ጥሩ ወጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል ብለዋል።

አትሌት መርደኪዮስ ወልዴ እና አትሌት ደራርቱ አኖታ የነበራቸው  ቆይታ ጥሩ እንደነረ በመግለጽ ጥሩ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ5 ወርቅ 4 የብር እና 1 የነሃስ ሜዳሊያ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

የአፍሪካ ሻምፒዮና ውድድሩ ከግንቦት 4 እስከ 9 ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ሲሆን ሽኝት የተደረገለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ግንቦት 2/20218 ዓ.ም እሁድ ጠዋት ወደ ስፍራው ያቀናል።

Categories: Uncategorized