ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረውየሁለተኛ ደረጃ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ አማካኝነት ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ፣ ባለሙያዎች ለአስር ተከታታይ ቀናት በኢንስትራክተር አሰፋ በቀለና እና ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት ሲሰጥ፣ የነበረዉ የሀገር ዉስጥ ሁለተኛ ደረጃ የዳኝነት ስልጠና ተጠናቋል።

ስልጠናው በተለያዩ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስርዓት ላይ በተለይም በታይም ትሮኒክስ ላይ ተመስርተው የተሰጠ ሲሆን በስፖርት ሳይንስ ውስጥ በትምህርት ደረጃቸው የመጀመርያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ላላቸዉ 25 ዳኞች የሀገር ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ስልጠና ተሰቷል።

ሰልጣኞቹ የተሰጣቸው የዳኝነት ስልጠና በተግባርና በንድፈ ሃሳብ የተደገፈ እና አሳታፊ በሆነ መንገድ በመሰጠቱ ስለ አትሌቲክስ ዳኝነት ያላቸው እውቀትና ግንዛቤ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። በዚህም በወሰዱት የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና እና እውቀት ከኢትዮጵያም አልፈው በአህጉርና ዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሰርቶ ሀገርን ለማስጠራት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ስልጠናውም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና አዲስ ሰልጣኞች ባገኙት እውቀት ሁሉንም የአትሌቲክስ ውድድሮች እንዲዳኙ መደረግ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የስልጠናና ምርምር ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ ስልጠናውን የወሰዱት ዳኞች በሙሉ ሁሉንም የሀገር ውስጥ ውድድሮች መዳኘት እንደሚችሉ ገልጸው፣ በወሰዱት ስልጠና ከውድድር ዳኝነት ሳይርቁ ውጤታማ እንዲሆኑ በሀገር አቀፍ በሚዘጋጁ ውድድሮች ውስጥ የዳኝነት ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ይደረጋል ብለዋል።

በዚህም ሰልጣኞቹ የቀደሙትን ዳኞች ለመተካትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዉጣት ሁሌም ዝግጁ መሆን እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።

የዳኞች ኢንስትራክተር፣ ሽመልስ ዳዊት እንዲሁ በተሰጠዉ ስልጠና መደሰታቸውን ገልጸዉ፣ ስልጠናዉን ለየት የሚያደርው፣ ሰልጣኞቹ በስፖርተ ሳይንስ የመጀመርያ ድግሪና ከዚያ በላይ ያላቸዉ መሆኑ፣ ውድድሮች በታይም ትሮኒክስ ተመዝግበው እና ዓለም አቀፍ እውቅናን ባገኙበት ወቅት መሆኑ እና ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የነሐስ ደረጃ ያለው ውድድር ስታዘጋጅ ሰልጣኞቹ ተገኝተው በአካል መሳተፋቸዉ መሆኑን ተናግረዋል። የስልጠና ዘይቤው ጥሩ እንደ ነበረና ብዙ ያልተፈቱ ጥያቄዎች የተፈቱበትና ከሀለተኛ ደረጃ በላይም እንደሆነ ጠቁመዋል።

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት፣ ኢንስትራክተር አቶ አድማሱ ሳጂ የኢ.አ.ፌ. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢና፣ ፌዴሬሽኑ በዳኝነትም ይሁን በአሰልጣኝነት የሀገር ዉስጥ ደረጃ አንድም ይሁን ደረጃ ሁለት የሰለጠኑ ዳኞች ብቁ ሆነው ስራ ላይ ሲቆዩ ወደ አለም አቀፍ ዳኝነት ማደግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የአሁኑን የዓይነት ስልጠና ለየት የሚያደርገዉ፣ የሰዓት መቆጣጠርያ ታይም ትሮኒክስ (Time tronicss) ከተለመደዉ የዳኝነት ስልጠና ወጣ ያለና በአብዛኛዉ ወደ ቴክኖሎጂ ያተኮረና በቂ የእዉቀት ሽግግር የተከናወነበት በመሆኑ ለሰልጣኞቹ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

ስልጠናውን የወሰዱት ሁሉም ሰልጣኞች በጥሩ ውጤት የምዘና ፈተናዉን የወሰዱ ያለፉ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ ተቀብለዋል።

Categories: Uncategorized