29ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ትልልቅ ውሳኔዎችን በመወሰን በስኬት ተጠናቀቀ

##########################

የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ በተቋሙ የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጀመረው ተቋማዊ ለውጥ መንግስት ለስፖርቱ ዘርፍ የሰጠው ትኩረት አንዱ አካል መሆኑን ገልጠዋል።

በጉባኤው የተሻሻለው የፌዴሬሽን የመተዳደሪያ ደንብ በጉባኤተኞቹ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ይህም ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን እና የተሻለ አደረጃጃት ለመዘርጋት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር በጉባኤው ተነስቷል።

ደንቡ በርካታ አዳዲስ ጉዳዮች ትኩረት ያካተተ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ የስልጣን ዘመን በሁለት ዙር የገደበ ነው ።

ከዚህ በተጨማሪ ከስራ አስፈፃሚ ከአባላት መካከል ቢያንስ አንዱ የቀድሞ አትሌት ፣ አሰልጣኝ ወይም የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ እንዲሆን ተወስኗል።

በጉባኤው በቀጣይ ፌዴሬሽንን ወደፊት ለማሻገር ያግዝ ዘንድ ተቋማዊ ሪፎርም እና የሰው ሃይል መዋቅራዊ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ፀድቋል።

ተቋማዊ ሪፎርሙ ፌዴሬሽኑን በሠው ሀይል እና በቴክኖሎጂ በማደራጀት ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን እንደሚያሻሽል በጉባኤው ተነስቷል።

የፌዴሬሽኑ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ቀርቦ በጉባኤው ላይ ቀርቦ ውይይት ሲደረግበት ማሻሻዎች ተደርገውበት ወደ ተግባር እንዲገባ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ የተሻሻለ የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎች ለጉባዔው አባላት ቀርበው ፀድቀዋል።

በጉባኤው የ2018 በጀት አመት የሥራ እቅድና በጀትን ፤ የ28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ፣የ2017 በጀት አመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ፣ የውጭ ኦዲተርን መሰየም እና የ2017 በጀት አመት የውጭ ኦዲት ሪፖርት ውይይት ተደርጎባቸው የፀደቁ ጉዳዮች ናቸው።

ባለፈው አንድ አመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የስራቸው ስራዎች ስኬታማ እንደነበሩ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል ።

Categories: Uncategorized