51ኛው ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ላለፉት 28 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊሲን አሻሽሏል።
አዲሱ የስፖርት ፖሊሲ የማህበረሰቡን ስፖርት ተሳትፎን የሚያረጋገጥ፣በቴክኖሎጅ የተደገፈ፣ጠንካራና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት፣እንድሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌደራል ስፖርት ልማትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በዝርዝር ተወያይቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።
እነዚህ የህግ ማዕቀፎች በኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር ላይ የተሻለ ስኬት እንድመዘገብና፣ መንግስት በዘርፉ የያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያግዙ መሆናቸው ተገልፆዋል ።