ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።

መጋቢት 6/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በዓመት ውስጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ማድረግ ነው።
የፌዴሬሽኑ
የስልጠና ጥናትና ምርምር ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ የስፖርት ትጥቁን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ለአካዳሚው አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለክልሉ ላበረከተው ድጋፍም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም መሠል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደስታ የተደረገው ድጋፍ በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ክልሉ ብቁ ሆኖ እንዲወጣ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ሀይሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ክልሉን በተለያዩ ጉዳዮች መደገፉን ገልጸው መሠል ድጋፎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል።

የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክሌ ነገሪ ማዕከሉ ተፎካካሪና ብቁ አትሌቲክሶችን ለማፍራት እንዲያስችለው የተደረገው ድጋፍ ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስልጠና ጥናትና ምርምር ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ከመስጠትም ባሻገር በስፖርት አካዳሚው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለበት ድረስ የተገኘውን ለውጥ የተመለከተ የሱፐርቪዥን ስራ በማከናወን እንዲሁም በክልሉ ያለውን የአትሌቲክስ ስፖርት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል ።

በተደረገው ርክክብ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አመራርና ባለሙያ፣የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች ፣ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ እና አሰልጣኞች ተገኝተዋል።

Categories: Uncategorized