በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
የካቲት 30/2018 ዓ.ም
በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት አሸንፋለች ።
አትሌት ፅጌ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1:04.48 ወስዶባታል።
አትሌት ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር በ1:07.30 5ኛ ወጥታለች።
በፈረንሳይ ዴ ሁካ ሰሚ ደ ፓሪስ የግማሽ ማራቶን አትሌት ፍታው ዘርኣይ በቀዳሚነት ውድድራን ፈፅማለች ።
አትሌቷ የገባችበት 1:05.12 የቦታው ምርጥ ሰዓት ነው።
ጃፓን ናጎያ ሴቶች ማራቶን አትሌት አይናለም ደስታ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በአምስት ወር ውስጥ ሁለተኛ ማራቶኗን የተካፈለችው አትሌት አይናለም ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2:22:37 ሰዓት ወስዶባታል፡፡

