የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድር ታሕሣሥ 05/2018 ዓ.ም በመቀሌ ለማድርግ በዝግጅት ላይ ይገኛል ስለሆነም በዚህ ውድድር ላይ ተወዳድረው ለሚያሸንፉት አትሌቶች ዳጎስ ያለ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ለክልሎች ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች እና ተቋማት የተወዳዳሪዎቻችሁን ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰብን የግል ተወዳዳሪዎች ጉርድ ሾላ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተሳ/ውድ/የሥ/ሂደት ክፍል ድረስ መታወቂያ ይዞ በመቅረብ 30/ሠላሣ/ ብር ብቻ በመክፈል የደረት ቁጥር ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን