የካቲት 3/2018 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ ገብተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባደረገላቸው ግብዣ መሠረት አዲስአበባ የገቡት ዳይሬክተሩ፣በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው

የአደይአበባ ዓለምአቀፍ የመለማመጃ ትራክ ስቴዲየም እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጎብኝተዋል።

ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣One day meeting ፣ ሌሎች ዓለምአቀፍ እና አህጉር አቀፍ

ለማዘጋጀት የሚያደርገው ዝግጅት፣የዳይሬክተሩ ጉብኝት አስፈላጊ መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን በተጨማሪም የስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነትን የሚያጠናክር ይሆናል።

ዳይሬክተሩ ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ፣ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ከፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውጤታማ ተወያይተዋል ።

Categories: Uncategorized