የካቲት 2/2018 ዓ.ም
ትናንት በፈረንሳይ ሜትዝ በተከናወነው የሴቶች 3ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትሎ በመግባት ድል ተጎናጽፏል ።
በዓለም አትሌቲክስ የብር ሜዳልያ በተሰጠው የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
አትሌት ብርቱካን ሞላ በ8:40.49 በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች ።
አትሌት ሽቶ ጉሜ በ8:41.18 2ኛ፣ አትሌት አስቴር አሬሪ በ8:41.75 3ኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትሎ ሲገቡ፣ አትሌት ቤተልሔም ኦላና 6ኛ ደረጃ ይዛ ውድድሩን አጠናቃለች።
በወንዶች ምድብ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በ7:44.83 ሶስተኛ፣አትሌት ኤርሚያስ ግርማ በ7:51.80 አምስተኛ፣ አትሌት ለሚ ተሾመ በ7:55.07 ሰባተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

