በ25ኛው የዱባይ ማራቶን በሴቶቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃን ይዘው አሸንፈዋል።
በሴቶቹ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ የግል ምርጥ ሰዓቷን በ4 ደቂቃ በማሻሻል አሸንፋለች።
የ23 አመቷ አትሌት ውድድሩን ያጠናቀቀችው 2: 22.17 በሆነ ሰዓት ነው ።
አትሌት ሙሉዬ ደቀቦ በ2:18:43 ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት ፋንቱ ወርቁ በ2:19:08 ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።
በወንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን የሮጠው አትሌት ንብረት መላክ አሸንፏል።
አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:04:00 ወስዶበታል ።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ያሲን ለጂ 2:05:52 ሁለተኛ ወጥቷል ።
በሪያድ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በቀዳሚነት አጠናቀዋል ።
አትሌት አበባው ሙንየ 2:09:30 በመግባት ሲያሸንፍ
አትሌት አሰፋ ተፈራ ሁለተኛ አትሌት ቶልቻ ተፈራ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶቹ አትሌት ኬና ግርማ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል አሸንፋለች።
አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ2 :25:54 ወስዶባታል።
አትሌት አበራሽ ደምሴ በ2:27:13 ሁለተኛ ፤ አትሌት ንግስት ሙሉነህ በ2:29:18 ሦስተኛ ወጥተዋል።
አትሌት ጀነራል ብርሃኑ በስፔን ቫሌንሽያ የነሐስ ደረጃ በተሰጠው የቤት ዉስጥ ዉድድር በ800 ሜትር አሸንፏል ።
አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1:46:61 ወስዶበታል።








