ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች !!

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ጥር 02/2018 ዓ.ም ታሃላሲ ፍሎሪዳ

በአሜሪካ ፍሎሪዳ በድምቀት የተከናወነው 46ኛው የአለም አገር አቋራጭ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል ።

የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

ፈታኝ እና ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት ውድድር ኢትዮጵያ በመድረኩ ባስመዘገቻቸው አጠቃላይ ሰባት ሜዳሊያዎች ኬኒያን ተከትላ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

485 አትሌቶች ከተለያዩ 52 የአለም ሀገራት በተፎካከሩበት ውድድር ምንም እንኳን በወጣት ወንድ አንድ አትሌት ብቻ እና በሴቶች ወጣት 3 አትሌቶች ብቻ በቪዛ ምክንያት ማሰለፍ ባለመቻላችን የቡድን ውጤት ሊመዘገብልን ባይችልም በተሰለፋት ልጆቻችን ኢትዮጵያ በሶስት የወርቅ፣በሁለት የብር እና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎች ነው በኬኒያ ብቻ ተበልጣ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በአዋቂ ወንዶች እና ሴቶች 10 ኪ.ሜ በቡድን ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ በመድረኩ ታሪክ ስትሰራ ፣ በአትሌት ማርታ አለማየው ወርቅ ፣በአዋቂ ወንዶች በአትሌት ሪሁ አረጋዊ እና በወጣት ሴቶች አትሌት ወሰኔ አሰፋ የብር ሜዳሊያ እና በድብልቅ ሪሌይ በቡድን የነሃስ በአዋቂ ሴቶች በአትሌት ሰናይት ጌታቸው የነሃስ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።

ሙሉ ቡድናችን እንዲመዘገብና ወደ ውድድር እንዲያቀና ለማድረግ ቢሞከርም ከታሰቡት ቋሚ 28 ተሰላፊዎች ያለቪዛ ችግር ማሰለፍ የቻልነው 14 ብቻ ሲሆን ይህም ከቋሚ ተሰላፊዎች 50% ያህሉን ብቻ ነው ማሰለፍ የቻልነው ።

ከዚህ አንጻር የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በሶስት ወርቅ በሁለት ብር በሁለት ነሐስ በሁለተኛ ደረጃ የተገኘው ውጤት ከፈተኛ ነው።

🇪🇹🇪🇹በመድረኩ ኢትዮጵያን ወክላችሁ ድል ላስመዘገባችሁ ብርቅዬ አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ።

🇪🇹እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

Categories: Uncategorized