6ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ሐሙስ ይጀመራል ።

#

(ኢ.አ.ፌ) የካቲት 24፣2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

6ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን ሐሙስ በአዲስአበባ ከተማ በአደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም ይጀመራል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሻምፒዮናውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

ሻምፒዮናው ከየካቲት 26-29/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በአደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም እንደሚካሄድ በመግለጫው ተመላክቷል።

ሻምፒዮናው በማሰልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ ወጣት አትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ ነው።

በ6ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ10 አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተውጣጡ 214 ሴቶች ፣ 248 ወንድ በአጠቃላይ 462 አትሌቶች ይሳተፋሉ።

ሻምፒዮናው በወንዶች 100 ሜ፣ 200ሜ፣400ሜ፣ 800ሜ፣ 1500ሜ፣ 5000ሜ፣10,000ሜ፣ ርዝመት ዝላይ፣ ከፍታ ዝላይ፣ሱሉስ ዝላይ፣ መዶሻ፣ ምርኩዝ ዝላይ ፣ጦር ውርወራ ፣ ድስከስ ውርወራ፣ አሎሎ ውርወራ፣ 4×100ሜ፣110 ሜ መሰናክል፣400ሜ መሠናክል፣ 3000ሜ መሠናክል ፣ 4×400ሜ ድብልቅ ረሌ ይካሄዳል።

በተመሳሳይ በሴቶች 100 ሜ፣ 200ሜ፣400ሜ፣ 800ሜ፣ 1500ሜ፣ 3000ሜ፣ 5000ሜ፣ ርዝመት ዝላይ፣ ከፍታ ዝላይ፣ሱሉስ ዝላይ፣ ጦር ውርወራ ፣ ድስከስ ውርወራ፣ አልሎ ውርወራ፣ 100ሜ መሠናክል፣ 400ሜ መሠናክል፣ 3000ሜ መሠናክል ፣ 4×100ሜ፣ 4×400ሜ
ድብልቅ ረሌ ሻምፒዮናው ይካሄዳል።

አቶ ጊዜ አድነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ እና የፌዴሬሽኑ የኮሚኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መሐሪ ነጋሽ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል።

ወቅታዊ እና ትኩስ የአትሌቲክስ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram : https://t.me/Ethiopian_Athletics_Federation
Facebook : https://www.facebook.com/EthiopianAthleticsFederation
Instagram: https://www.instagram.com/ethiopian.athletics/?hl=en
Twitter : https://twitter.com/eaf_ethio
YouTube : https://www.youtube.com/@EthiopianAthleticsFederation1
website :https://www.eaf.org.et

Categories: Uncategorized