6ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ በአዲስአበባ በድምቀት ይጀመራል

#

የካቲት 25፣2018 ዓ.ም

6ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ሐሙስ 26/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በአደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም ይጀመራል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ እና ኢንስትራክተር ሽመልስ ዳዊት
የሻምፒዮናውን ቅድመ ዝግጅት(Pre match ) አስመልክቶ ከማዕከላት ቡድን መሪዎች ፣አሰልጣኞች እና አትሌቲክስ ዳኞች ጋር ውይይት አድርጓል ።

ሻምፒዮናው በማሰልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ ወጣት አትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል ።

በሻምፒዮና ከ10 አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተውጣጡ 214 ሴቶች ፣ 248 ወንድ በአጠቃላይ 462 አትሌቶች ይሳተፋሉ።

ሻምፒዮናው በወንዶች 100 ሜ፣ 200ሜ፣400ሜ፣ 800ሜ፣ 1500ሜ፣ 5000ሜ፣10,000ሜ፣ ርዝመት ዝላይ፣ ከፍታ ዝላይ፣ሱሉስ ዝላይ፣ መዶሻ፣ ምርኩዝ ዝላይ ፣ጦር ውርወራ ፣ ድስከስ ውርወራ፣ አሎሎ ውርወራ፣ 4×100ሜ፣110 ሜ መሰናክል፣400ሜ መሠናክል፣ 3000ሜ መሠናክል ፣ 4×400ሜ ድብልቅ ረሌ ይካሄዳል።

በተመሳሳይ በሴቶች 100 ሜ፣ 200ሜ፣400ሜ፣ 800ሜ፣ 1500ሜ፣ 3000ሜ፣ 5000ሜ፣ ርዝመት ዝላይ፣ ከፍታ ዝላይ፣ሱሉስ ዝላይ፣ ጦር ውርወራ ፣ ድስከስ ውርወራ፣ አልሎ ውርወራ፣ 100ሜ መሠናክል፣ 400ሜ መሠናክል፣ 3000ሜ መሠናክል ፣ 4×100ሜ፣ 4×400ሜ ድብልቅ ረሌ ሻምፒዮናው ይካሄዳል።

Categories: Uncategorized