4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶች አትሌት ንብረት ክንዴ ፣ በሴቶች አትሌት ብርቱካን ሞላ አሸነፉ።
ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም
መነሻ እና መድረሻው መስቀል አደባባይ ያደረገው ኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ዛሬ በታላቅ ድምቀት ተከናውኗል ።
በወንዶች ምድብ አትሌትንብረት ክንዴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ ሆኗል ።
አትሌት ጀንበሩ ሲሳይ በግል ሁለተኛ አትሌት ግዛቸው ሙሴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሦስተኛ ደረጃን በቅደም ተከተል ወጥተዋል።
በሴቶቹ አትሌት ብርቱካን በግል አሸንፋለች ።
አትሌት ሮቤ ዲዳ እና አትሌት ኑሪት አህመድ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል ።
4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር ላይ ከክለቦች እና ተቋማት የተውጣጡ ከ500 በላይ አትሌቶች ተካፍለዋል ።
በውድድሩ በሁለቱም ፆታ አንደኛ በመሆን ላጠናቀቁ አትሌቶች 550 ሺህ፣ 2ኛ ለወጡ 300 ሺህ እንዲሁም 3ኛ በመሆን ላጠናቀቁ 200 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል።




