የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር ፣መካከለኛ ፣የ3000 ሜትር መሰናክል የርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ ።
#######################################################################
ታህሳስ 26/2017
ለተከታታይ አምስት ቀናት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣መካከለኛ ፣የ3000 ሜትር መሰናክል ርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድምር ውጤት አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።
ሻምፒዮናው ከታህሳስ 22-26/2017 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በድምር ውጤት ኢትዮጵያ ንግድ በአንደኝነት ፣መቻል ሁለተኛ እንዲሁም ሸገርሲቲ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ሲጠናቀቅ፤
በአጠቃላይ አሸናፊ:-
በሴት
1ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 180.5
2ኛ መቻል 155.5
3ኛ ሸገርሲቲ እና ሲዳማ ቡና 72.5
በወንድ
1ኛ መቻል 159.5
2ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 138.5
3ኛ ሸገር ሲቲ 89.5
በአጠቃላይ ድምር ውጤት
1ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 319
2ኛ መቻል 315
3ኛ ሸገርሲቲ 162
በሻምፒዮናው ፍፃሜ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።