ለሶስት ተከታታይ ቀናት በደሴ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጠኞች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታኅሣሥ 25 /2017 ዓ.ም ደሴ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደሴ ከተማ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ማለትም ከታኅሣሥ 23-25 /2017 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጣኝ መምህራን ስልጠና በስኬት ተጠናቋል ።
በመጨረሻው የህፃናት አትሌቲክስ (kid’s Athletics ) የተግባር የአሰልጠኞች ስልጠና በጥሩ ሁኔታ የተሰጠ ሲሆን እድሜያቸው 8-12 ያሉት ተማሪዎች በቡድን በማድረግ በጨዋታ መልክ ተማሪዎችን በቀረበው የአትሌቲክስ ቁሳቁስ ስልጠናውን መስጠት ተችሏል ።
በስልጠናው ላይ የተካፈሉ መምህራን:- ፌዴሬሽኑን በማመስገን ከስልጠናው ጥሩ እውቀትና ልምድ እንዳገኙ በመግለፅ የሰለጠኑትን ወደተግባር በመቀየር እንደሚሰሩ የተናገሩ ሲሆን በቀጣይ ቤሄራዊ ፌዴሬሽኑ፣ የክልሉ ፌዴሬሽንና የከተማው ስፖርት መምሪያ በሌሎች ትምህርት ቤቶች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በመቀጠል ኢንስትራክተር አቶ አድማሱ ሳጂ የኢ.አ.ፌ. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ባስተላለፉት መልእክት :-
የህፃናት አትሌቲክስ ላይ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተባብረን ተደጋግፈን ከሰራን ለሀገር ያለው ፋይዳ የላቀ እንደሆነ በመግለፅ ለሰልጣኞቹ ህፃናትን መመልመል እና ማሰልጠን ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል አክለውም ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በማገዝ በሱፐርቪዝን አብሮ እንደሚሰራ በመግለፅ ስልጠናውን በሌሎች ከተሞችና ክልሎች ላይ በ2017 ዓ.ም ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም ለሰልጣኞቹ የሰርተፍኬት አሰጣጥ መርኃግብር ተከናውኗል።