የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአጭር ፣መካከለኛ ፣3000 ሜትር መሠናክል ፣ሜዳ ተግባራትና የርምጃ ውድድር ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
#############################################################
ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ የአጭር፣መካከለኛ ፣የ3000 ሜትር መሠናክል ፣የሜዳ ተግባራትና ርምጃ ውድድር ዙሪያ ለመገናኛ ቡዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።
መግለጫው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሙኒኬሽን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሀንስ እንግዳ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ በጋራ ተሰጥቷል ።
በውድድሩ 21 ክለቦች፣ 2 ከማሰልጠኛ ማዕከላት፣ 1 ከአካዳሚ በአጠቃላይ 24 ተቋማት በተጨማሪም 331 ሴት ፣416 ወንድ በድምሩ 747 አትሌቶች እንደሚሳተፉ እና ውድድሩ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከታህሳስ 22-26/2017 ዓ.ም በጠዋት መርሀግብር እንደሚካሄድ በመግለጫው ተጠቁሟል ።