የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ አትሌት መሰረት ደፋርን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

#############################################################

ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡ የሚታወስ ነው።

በጉባኤው የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያ ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ።

በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት እና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል ።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጨምሮም የተለያየ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን :-

👉ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ አቃቤ ንዋይና የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ ቢኒያም ምሩፅ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ወይዘሮ ሳራ ሀሰን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሃብት አሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ አድማሱ ሳጂ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስነምግባርና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ኢፍራህ መሀመድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

👉አትሌት የማነ ፀጋይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በማድረግ ስብሰባውን አጠናቀዋል ።

Categories: Uncategorized