ታኅሳስ 12፣ 2017ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በስካይላይት ሆቴል የክብር እንግዶች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።
በጉባዔው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ በመልዕክታቸው ከስፖርት ውጤታማነት አንፃር በተለይም በኦሎምፒክ መድረክ የሚገኘው ወርቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ በስፖርቱ አፍቃሪ ማህበረሰብ ዘንድ ጥያቄዎችን አስነስቷል ያሉት ሚኒስትሯ ላለፉት አመታት የህዝብን አደራ ተቀብለው ስፖርቱን በመምራት ላይ ለነበሩ ለረዳት ኮሚሽነር ደራረቱ ቱሉ እና ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
በጠቅላላ ጉባኤ ለሚሳተፋ አካላት አትሌቲክስ ስፖርት ወደ ቀድሞ ከፍታው በሚመልስ ሁኔታ ላይ በጥልቀት በመወያየት ዲሞክራሲያዊ ፍትሀዊና ከምንም ተፅዕኖ ነፃ በመሆን በቀጣይ ፌዴሬሽኑን በዕውቀት የሚመሩ ኢትዮጵያን የሚወከሉ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲመርጡ ከአደራም ጭምር ጋር ጠይቀዋል።
በአዲስ የሚመረጡ አመራሮችም ህዝብ የሚጠብቅባችሁን ሀላፊነት በመወጣት ለላቀ ውጤት እንደምትበቁ ያለንን እምነት እገልፃለሁ ብለዋል።
በጉባዔው የኤ.አ.ፌ የአራት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ27ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ፣ የ2016 በጀት አመት የስራ ዕቅድ አልፃፀም ሪፖርት፣ የኦዲት ሪፖርት፣ የ2017 በጀት አመት እቅድና በጀት ቀርቦ ተመርምሮ ይጸድቃል። የባለ ድርሻ አካላት የእውቅና ፕሮግራ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እውቅና የስራ አስፈጻሚ ምርጫ፣ የዕጩዎች ፕሮፍይል ርክክብ እና ቃሉ መሀላ፣ የዕጩ ፕሬዚዳንቶች ፕሮፋይል ማቅረብ በዕለቱ የሚከውኑ እንደሆነ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።