በደሴ ከተማ የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጠኞች ስልጠና የሁለተኛው ቀን መርኃግብር በተሳካ ሁኔታ ተሰጥቷል ።

******************************

ታኅሣሥ 24/2017 ዓ.ም ደሴ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደሴ ከተማ የህፃናት አትሌቲክስ (kid’s Athletics ) የአሰልጠኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

በሁለተኛው ቀን የስልጠና መርኃግብር ላይ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተካፈሉ ሲሆን በጠዋቱ መርኃግብር :-

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ ምንድነው?

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ አላማው

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ እንደሀገር ያለው ጠቀሜታ

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ ተሰጦን መለየት

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ ስልጠና መርሆች

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ ( safeguarding) ጥበቃ እና ደህንነት

🔷 በምን መልክ ህፃናት የአትሌቲክስ እንቅስቃሴን ማሰራት እንችላለን በሚሉ የተለያዪ ርእሰ ጉዳዬች ላይ በስፋት እና በጥልቀት ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን

በከሰአቱም መርኃግብር :-

🔷 የህፃናት አትሌቲክስ የስልጠና ቁሳቁሶች ትውውቅ እና እንዴት አስመስሎ መስራት እንደሚቻል

🔷እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በተግባር ስልጠናውን መስጠት ተችሏል።

👉🏾 የተግባር የህፃናት አትሌቲክስ የአሰልጠኞች ስልጠና በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል ።

Categories: Uncategorized