የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር ፣መካከለኛ ፣የ3000 ሜትር መሰናክል የርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ቀን መርሀግብር ተከናውኗል ።

##############################################################

ታህሳስ 24/2017

ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣መካከለኛ ፣የ3000 ሜትር መሰናክል ርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተከናውኗል ።

በዚህም መሰረት የተለያዩ የፍፃሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን :-

👉አሎላ ውርወራ ሴቶች

1ኛ ዙርጋ ኡስማን-መቻል-13.27ሜ-ወርቅ

2ኛ አመለ ይበልጣል -መቻል-12.57ሜ -ብር

3ኛ ስምረት አበበ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-12.13ሜ-ነሀስ

👉አሎሎ ውርወራ ወንድ

1ኛ ነነዊ ኢንቶቦ -መቻል-15.77ሜ-ወርቅ

2ኛ ሞክሪያ ሀይሌ-ሸገርሲቲ-14.33ሜ-ብር

3ኛ ዘገየ ሞጋ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-14.16ሜ-ነሀስ

👉ከፍታ ዝላይ ሴቶች

1ኛ ፓች ኡመድ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-1.80ሜ-ወርቅ

2ኛ በፀሎት አለማየሁ -መቻል-1.75ሜ-ብር

3ኛ አርአያት ዲቦ- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ -ነሀስ

👉100ሜ ወንድ

1ኛ ቢኒያም ፊሊጵስ -ሲዳማ ቡና-10″31 -ወርቅ

2ኛ አጁሉ ኩሉ -ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ -10″34-ብር

3ኛ ሎፕ ኪያንግ-ሲዳማ ቡና -10″40-ነሀስ

👉100ሜ ሴቶች

1ኛ ያአብስራ ጃርሶ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-11″82-ወርቅ

2ኛ መሰረት ጉዲራ-ሲዳማ ቡና-12″17-ብር

3ኛ ስመኝ ተመስገን -ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-12″37-ነሀስ

👉ስሉስ ዝላይ ሴቶች

1ኛ ፓች ኡመድ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-13.28ሜ-ወርቅ

2ኛ በፀሎት አለማየሁ -መቻል-12.42ሜ-ብር

3ኛ ዱርሲቱ ጫኩኔ-አዳማ ከነማ-12.36ሜ-ነሀስ

በሻምፒዮናው ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቢ ነዋይ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ሳራ ሀሰን፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ እንግዳ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ማስተዋል ዋለልኝ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች

ተገኝተዋል ።

ሻምፒዮናው ነገም በተለያዩ ውድድሮች የሚቀጥል ይሆናል።

Categories: Uncategorized