የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከነገ ጀምሮ የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነትና ዳኝነት ስልጠና ሊሰጥ ነው።
##################################################
ጥር 06/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነትና ዳኝነት ስልጠና ዙሪያ ዛሬ በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የስልጠና፣ጥናትና ምርምር ሰብሳቢ ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ ፣የኢ.አ.ፌ ጵ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ እና የኢ.አ.ፌ. የስልጠና ፣ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ በጋራ በመሆን ለመገናኛ ቡዝኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ስልጠናው ከጥር 7-የካቲት 7/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የሚሰጥ ሲሆን፣የአገር ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ስልጠና ወስደው የላቀ ውጤት ያላቸውን አሰልጣኝና ዳኞችን የአለምአቀፍ ስልጠና በመስጠት በዘርፉ ያሉትን የአሰልጣኝነት እና ዳኝነት ክፍተቶችን ለመሙላት ዓላማ ያደረገ እንደሆነ በመግለጫው ተጠቁሟል ።
በአጠቃላይ 48 የአሰልጣኝነት እንዲሁም 20 በዳኝነት ስልጠናውን የሚወስዱ ሲሆን፣ስልጠናው ኢትዮጵያዊ በሆኑ ሶስት የዓለም አትሌቲክስ ኢንስትራክተሮች የሚሰጥ ይሆናል።
ስልጠናው ከሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለተውጣጡ አካላት የሚሰጥ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫ ተመልክቷል ።