የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለአመታት ተከማችቶ የነበረውን የሠራተኞች አለመግባባት ችግር በውይይት ሙሉ በሙሉ በመፍታት ደማቅ ታሪክ ፅፏል።
#################################l
ጥር 03/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ጥር 04/2017 ዓ.ም ከፌዴሬሽኑ ሠራተኞች ጋር ከረጅም ዓመታት በኃላ ግልፅ የሆነ የመጀመሪያውን ውይይት አድርጓል ።

ፕሬዚዳንቱና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በየ ስራሂደቱ የተከናወኑ ተግባራት ከገመገመ ብኃላ ለቀጣይ 100 ቀናት የሚሰሩ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመወያየት እቅዱን ገምግሟል ።

ፕሬዚዳንቱና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በመቀጠል ለአመታት ተንሰራፍቶ የነበረውን የሰራተኞች የውስጥ ችግር ሰፊ ስዓት በመውሰድ ውይይት አድርጓል ።

ፕሬዚዳንቱና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለስራ ተግዳሮት የነበሩ ማነቆዎች በመፍታት ሠራተኛውን በይቅርታ እና በፍቅር እንዲያምን በማድረግ በፌዴሽኑ ሲስተዋሉ የነበሩት አለመግባባቶች በእርቅ በመፍታት ደማቅ ታሪክ ፅፏል።

በተለይ በሠራተኛው የነበረው አለመግባባት እስከ ፍርድቤት የሄደ ጉዳይን ያካተተ ሌሎች ተያያዥ ተግዳሮቶች በውይይት እንዲፈታ ተደርጓል ።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቀጣይም የግንኙነት ጊዜ በማስቀመጥ ስራዎችን እየተገመገሙ እንዲሄዱ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

የፌዴሬሽኑ ሰራተኞች ፕሬዚዳንቱና ሰራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግዜ ሰጥቶ በፌዴሬሽኑ ተንሰራፍቶ የቆየውን ስር የሰደደ የሰራተኞች ችግር በዚህ መልክ እንዲፈታ በማድረጉ በውይይቱ መጨረሻ ላይ እንባ በተቀላቀለ ስሜታቸውን በመግለፅ የጋራ መግባባት በመፍጠር ስብሰባው ተጠናቋል ።