ኦሮሚያ ባንክ ለአዲሱ ተመራጭ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

ጥር 04/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስፖንሰር ከሆኑ መካከል አንዱ የሆነው ኦሮሚያ ባንክ ለአዲሱ የፌዴሬሽኑ ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ ።

ኦሮሚያ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባከናወነው 28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የፌዴሬሽኑ
ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩት አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁኖው ለተመረጡት አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የተሰማውን ደስታ ገልጿል ።

በቶፕ ቴን ሆቴል በተከናወነው መርሀግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ባንክ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴድሮስ ኃይሉ አትሌቲክስ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በዓለም ላይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ከፍተኛ ሚና መጫወቱ በመጦቀም ቀጣይም አጋርነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው ኦሮሚያ ባንክ ለአትሌቲክሱ እድገት እና አጋርነት ያበረከተውን አስተዋጽኦ በማመስገን ድጋፋ ቀጣይ እንዲሆን በማሳሰብ ፣በቀጣይም በአብሮነት እንደሚሰሩ አንስቷል ።

ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው።

Categories: Uncategorized