በፈጣን አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ለሕዝብ አገልግሎት እንካችሁ ብለናል! ለዜጎቻችን ጤና እና ለከተማችን ዕድገት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠው ይህ ስራ፤ ከፕሮጀክት የተሻገረ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ ነው!

ለሁሉም ዜጋ የተገነባው ይህ ማዕከል የሚከተሉትን አካቷል፦

‎• 5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፤

‎• የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃት በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አትሌቶቻችን የክብር ሐውልቶች፤

‎• ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች፤ የኦሎምፒክ ደረጃን የሚያሟሉ የመዋኛ ገንዳ፣ የ800 ሜትር የሩጫ ትራክ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች፣ የልጆች መጫወቻዎች እና አሸዋ የተዘረጋበት ስፍራ፤

• ለማህበረሰቡ፦ ለነጋዴዎች የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆች እና 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ ተካተውበታል።

‎የተሻለች ኢትዮጵያን ማለም ብቻ ሳይሆን እኛ በተግባር እንገነባታለን!

Delivered in record time, the Addis Sports Park is now officially yours! More than just a project, this is a powerful testament to our commitment to public wellness and urban progress, it is the true face of the New Ethiopia!

A hub designed for every citizen:

• 5.7 Hectares of world-class sports and green recreational space.

• 15 Honorary Statues of our Olympic gold medalists to inspire the next generation.

• Elite Facilities: Olympic-standard pool, 800m track, and professional courts for football, basketball, tennis, playground for children and sand pitches.

• Community Impact: 105 new shops for local traders and a grand plaza for 3,000 people.

We don’t just envision the future, we build it!

#EthiopiaDelivers

#PMOEthiopia

No insights to show

Categories: Uncategorized, ዜና