6ኛዉ የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በደራርቱ ቱሉ ማሰልጠኛ ማዕከል አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

###################

የካቲት 29/2018 ዓ.ም

ለተከታታይ አራት ቀናት በአደይ አበባ ዓለምአቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ የደራርቱ ቱሉ ማሰልጠኛ ማዕከል በ332 ነጥቦች አሸናፊ ሆነ።

ሀገረሰላም በ320 ነጥቦች እና ተንታ 276 ነጥቦች ማሰልጠኛ ማዕከላት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በወንዶች ሀገረሰላም በ186.5 ነጥቦች በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ፤ ደራርቱ ቱሉ ማሰልጠኛ ማዕከል በ179.5 ነጥቦች ሁለተኛ ተንታ ማሰልጠኛ ማዕከል በ124.5 ነጥቦች ሦስተኛ ወጥቷል።

በሴቶች ደራርቱ ቱሉ ማሰልጠኛ ማዕከል በ152.5 ነጥቦች አንደኛ ፤ ተንታ በ151.5 ነጥቦች እና ሀገረሰላም ማሰልጠኛ ማዕከላት በ133.5 ነጥቦች በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል።

በውድድሩ ከ10 አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተውጣጡ 214 ሴቶች ፣ 248 ወንድ በድምሩ 462 አትሌቶች ተካፍለዋል።

የአራተኛው ቀን የፍፃሜ ውጤት :-

🔹4X100 ሜ. ሴት

1ኛ ተንታ 50.87

2ኛ ሀገረሰላም 51.25

3ኛቨጂንካ 51.64

🔹4X100 ወንድ

1ኛ ደራርቱ ቱሉ 42.90

2ኛ ተንታ 43.64

3ኛ ጂንካ 44.56

🔹4X400 ድብልቅ ሪሌ ወ/ሴ

1ኛ ሀገረሰላም 3:30.79

2ኛ ደራርቱ ቱሉ 3:32.29

3ኛ በቆጂ 3:36.50

🔹ከፍታ ዝላይ

1ኛ በጥሶ ቱሜቻ ሀገረሰላም 1.97

2ኛ ዳንኤል ሸለመ ደራርቱ ቱሉ!1.95

3ኛ በንቲ ገ/ማርያም ደራርቱ ቱሉ 1.95

🔹400 ሜ.መሠ. ወንድ

1ኛ አያሌው በሬሣ ሀገረሰላም 52.77

2ኛ ፍቃዱ መንጦ ሀገረሰላም 54.89

3ኛ ኢዩኤል ዱብአለ ሀገረሰላም 55.17

🔹400 ሜ.መሠ ሴት

1ኛ መስከረም መለሰ ሀገረሰላም 1:01.27

2ኛ ገነት ፍቃዱ ቦሬ 1:06.07

3ኛ ሰርክአዲስ በላይ ተንታ 1:07.07

Categories: Uncategorized