ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኘው የአትሌቲክስ ውድድር በሀዋሳ ከተማ !
#
በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የካቲት 7/2018 ዓ.ም ይካሄዳል ።
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛው አመቱን በድምቀት ሀዋሳ ከተማ ላይ የሚያከብር ሲሆን፣በዓሉ ከሚከበርባቸው ሁነቶች መካከል የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አንዱ ነው።
በዚህም መሠረት :-
1ኛ ለሚወጡ 500 ሺህ ብር
2ኛ ለሚወጡ 250 ሺህ ብር
3ኛ ለሚወጡ 100 ሺህ ብር እና እስከ 5ኛ ለሚወጡ አትሌቶች ሽልማቱ ይበረክትላቸዋል።
የዚህ ታሪካዊ ሩጫ የመሮጫ ትሸርቱን በሀዋሳ (በሁሉም ንግድ ባንኮች) እና በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ያገኙታል።
በተጨማሪም ለአትሌቶች የደርሶ መልስ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል ።
አርብ የካቲት 6 ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ከአዲስ አበባ ይነሳል ፣ በማግስቱ ቅዳሜ ከውድድሩ በኋላ 7:00 ሰዓት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል።
ለአትሌቶች ምዝገባ ጃንሜዳ አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ሀዋሳ በሲዳማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኙታል ።
ለበለጠ መረጃ በ 0945627777 ይደውሉ ።

