የሁለተኛው ዙር የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና የምርቃት መርሀግብር ተከናወነ::

*************************************

የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና የሁለተኛው ዙር የምርቃት መርሀግብር አከናውኗል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበጀት ዓመቱ በእቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው በርካታ የልማት ተግባራት መካከል አንዱ እና ዋነኛው ስልጠና ሲሆን፣ በዛሬው እለትም በሁለተኛው ዙር የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና 14 ሴት 10 ወንድ በድምሩ 24 አሰልጣኞች ተመርቀዋል።

በመርሀግብሩ ላይ ለተመራቂዎች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ፤ ስለነበረው የስልጠና ቆይታ የተመራቂ ተወካዮች በስፋት አብራርተዋል ።

ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር አቶ አድማሱ ሳጂ የኢ.አ.ፌ. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሀኑ የኢ.አ.ፌ. የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ያገኝቱን ልምድ፣ እውቀትና ተሞክሮ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል ።

በምርቃት መርሀግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ንዋይ፣ የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ

ለተመረቁ ሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ስልጠናው በሃገር ውስጥ መሰጠት መቻሉ አውንታዊ ፋይዳ እንዳለው በመጠቆም ፣

በተለይም ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው በዚህ ዙር የሴቶች ቁጥር በዛ ያለ መሆኑ ሴቶች እድሉን ካገኙ መስራት እንደሚችሉ ማሳያ ነው ፤ የሀገራችን የአትሌቲክስ ውጤት የተመዘገበው በአብዘኛው በሴቶች መሆኑን አንስተዋል ።

በተጨማሪም ፣

ተመራቂዎች ያገኛችሁን እውቅና ልምድ ወደ መሬት አወርዳቹ ተተኪ አትሌቶችን እንድታፈሩ አሳስባለው ብለዎል::

Categories: ዜና