የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀዋል ።
#####################################################
ጥር 22/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የፊታችን እሁድ 25/2017 ዓ.ም በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል ።
ፌዴሬሽኑ ዛሬ በቤልቪው ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን በሻምፒዮናው ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ እና የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ በጋራ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የሻምፒዮናው ዓላማ አትሌቶች በአገር ውስጥ የውድድር እድል እንዲያገኙ ለማድረግ፣ክልሎች ፣ከተማ አስተዳደሮችን፣ክለቦችንና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት በጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍ የእርስ በእርስ የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እድል ለመፍጠር መሆኑን በመግለጫው ተጠቁመዋል ።
በሻምፒዮናው ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሻገር የኬንያ እና የሱዳን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፣በውድድሩ ላይም የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣አምባሳደሮች ፣የቀድሞ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ታዋቂና አንጋፋ አትሌቶች ፣የሚድያ አካላት ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ በመግለጫው ላይ ተብራርቷል ።



