የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና መስጠት ጀመረ።

##############################################################

ጥር 7/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መስጠት ጀመረ።

በስልጠናው መክፈቻ መርሀግብር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን ፣የመክፈቻ ንግግር እና የስራ መመሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ስለሺ ስህን ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን በማንሳት ፌዴሬሽኑ ከዓለም አትሌቲክስ ፣ከአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ፣ከአፍሪካ አትሌቲክስ ዴቨሎፕመንት ሴንተር ጋር ባለው መልካም የስራ ግንኙነት የተገኘ እድል መሆኑን ጠቁመዋል ።

ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ስልጠናው በሶስት ኢትዮጵያውያን ኢንስትራክተሮች መሰጠቱን አሞካሽቶ ስልጠናው በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ የታገዘ መሆኑን በማከል ሰልጣኞች የሚያገኙት ትምህርት፣ልምድና ተሞክሮ ለቀጣይ ስልጠና የሚጠበቅባቸውን ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ መስራት እንዳለባቸው በማሳሰብ መልካም ምኞታቸውን ለአሰልጣኞች ገልፀውላቸዋል ።

ስልጠናው ከጥር 7/2017 ዓ.ም -የካቲት 7/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣የመጀመሪያው ዙር አሰልጠኝነት ስልጠና ከጥር 7-18 2017 ዓ.ም ፣የዳንኝነት ስልጠና ከጥር 14-18 /2017 ዓ.ም እንዲሁም ፣ሁለተኛው ዙር አሰልጣኝነት ስልጠና ከጥር 26-የካቲት 7 2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተወጣጡ ሰልጣኞች ተሳታፊ ይሆናሉ።

Categories: Uncategorized