ጥር 25/2017 ዓ.ም

42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በታላቅ ድምቀት እና በስኬት ተጠናቋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያከናወነው 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ፣አትሌቶች በአገር ውስጥ የውድድር እድል እንዲያገኙ ለማድረግ፣ክልሎች ፣ከተማ አስተዳደሮችን፣ክለቦችንና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት በጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍ የእርስ በእርስ የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እድል ለመፍጠር ፣በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች በሽልማት ለማበረታታት ዓላማ ያደረገ ሻምፒዮና ነው።

በዚህም መሰረት

👉ድብልቅ ሪሌ

1ኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

2ኛ ኦሮሚያ ክልል

3ኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

👉6 ኪ.ሜ ወጣት ሴቶች

1ኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

2ኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

3ኛ ሸገር ሲቲ

👉8ኪ.ሜ ወጣት ወንዶች

1ኛ ሸገር ሲቲ

2ኛ አማራ ክልል

3ኛ ጥሩነሽ ዲባባ

👉10 ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች

1ኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

2ኛ ኦሮሚያ ፖሊስ

3ኛ አማራ ክልል

👉10 ኪሜ አዋቂ ወንዶች

1ኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

2ኛ ኦሮሚያ ክልል

3ኛ መቻል

በመሆን ሻምፒዮናው አጠናቋል ።

በሻምፒዮናው የተሳተፋ አካላት

👉ክልል -6

👉ከተማ አስተዳደር -2

👉ክለቦችና ተቋማት -29

👉ቬትራን በሶስቱም ካቴጎሪ

👉የግል ተወዳዳሪዎች -177

👉ኬንያ-2

👉ሱዳን-2

👉የገንዘብ ሽልማት መጠን በየውድድሩ ካታጎሪው የተቀመጠ ሲሆን በአጠቃላይ 865,000 ብር

👉በሰው ሃይል ውድድሩን ለመምራት በቴክኒክ ፣በአስተዳደር ፣በኮሚኒኬሽን ፣በዳኝነት ፣በህክምና እና በሌሎች አገልግሎቶች ውድድሩን ለማካሄድ ከ190 በላይ የሰው ሃይል ተሰማርተዋል ።

👉ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ለማከናወን በአጠቃላይ ወደ 4 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ወጪ አድርጓል ።

👉ሻምፒዮናው በኢቲቪ መዝናኛ፣ በኢቲቪ ዜና ቻናሎች እንዲሁም በኢቢሲ ዶትስትሪም ከማለዳው 1:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አግኝቷል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው በግላቸው ባሰባሰቡት 700,000 ብር ተጨማሪ ለአትሌቶች ሽልማት እንዲሰጥ አድርጓል ።

በሻምፒዮናው ላይ በአለም አቀፍ አትሌቲክስ የዉድድር ኮሚሽን አባል ፣የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባልና የምስራቅ አፍሪካ ሪጅን አትሌቲክስ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ኢንጂነር ሳዲቅ ኢብራሂም ፣የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣የኦሮሚያ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣አምባሳደሮች ፣የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር አመራሮች ፣የሚድያ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

Categories: Uncategorized