የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
###########################################
የካቲት 15/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሁለተኛ ዙር የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየሰጠ ይገኛል ።
ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ሁለተኛ ዙር በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ይገኛል ።
ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተወጣጡ 24 ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ላይ ከሰልጣኞች መካከል 60% ሴቶች ናቸው።
ስልጠናው በኢትዮጵያውያን ኢንስትራክተሮች ፣ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ እና ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ እየተሰጠ ይገኛል ።
ስልጠናው እስከ የካቲት 24/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ።




