የአፋር ክልል ባህል፣ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ከክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ እና ዳኞች ማህበር ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና የሀገር ውስጥ አንደኛ ደረጃ ላላቸው የአፋር ክልል ዳኞች በአፋር ክልል አብኣላ ከተማ መስጠት ጀምረ።

የክልሉን የአትሌቲክስ ዳኞችን ቁጥር ለማሳደግ እና በክልል ደረጃ የሚደረጉ ውድድሮችን በከፍተኛ ብቃት መዳኘት እንዲያስችላቸው በማሰብ የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በሆኑት አቶ አዲሱ ካሳ አስተባባሪነት 30 ለሚሆኑ የክልሉ ዳኞች የሁለተኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ የአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና በአፋር ክልል ኪልበቲረሱ ዞን አብአላ ከተማ መስጠት ተጀምሯል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱልን የአብኣላ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ወጣቶች ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የወቅቱ የአፋር ክልል አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ አብደላ አሚን ሲሆኑ ስልጠናውን በሚገባ በመከታተል የክልላችንን የአትሌቲክስ ዳኝነት በአንድ ደረጃ ከፍ እንዲያደርጉ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሰጠንን እድል በሚገባ እንድንጠቀም አሳስበዋል።

ስልጠናውን የክልሉ ባህል፣ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ከክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ለስልጠናው መሳካት የተከበሩ አቶ አሊ ጊልሳ የአብአላ ሆስፒታል ሀላፊ(አዳራሽ በመስጠት)፣ አቶ ኑሩ አሚን የአሳአሌ ኮሌጅ ምክትል ሀላፊ(ፕሮጀክተር በመስጠት) ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ስልጠናውን የኢትዮጵያ እና የክልሉ የአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ፕሬዚዳንት በሆኑት እና የአለምአቀፍ 1ኛ ደረጃ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ የዳኝነት ስልጠና ያለፉትና በተጨማሪም በRace walking የbronze level የዳኝነት ደረጃ ላይ በሚገኙት አቶ አዲሱ ካሳ እና የኢትዮጵያ እና የክልሉ የአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትና የአለምአቀፍ 1ኛ ደረጃ የዳኝነት ሰርተፍኬት ባላቸው እንዲሁም ለአለም አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ባለፉት ወ/ሮ ማህሌት ሹሜ አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል።

ስልጠናው ከጥር 28-የካቲት 7/2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

Categories: Uncategorized