ዛሬ በተከናወኑ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፏል ።
የካቲት 16/2017 ዓ.ም
በ2025 ኮርያ -ዴጉ ኢንተርናሽናል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በአለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር በሴቶች አትሌት መሰረት በለጠ በአንደኝነት አሸንፋለች ።
አትሌት መሰረት ርቀቱን ለማሸነፍ 2:24:08 ወስዶባታል።
አትሌት ትግስት ግርማ 2:26:45 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በወንዶች አትሌት አዲሱ ጎበና በ2:05:24 ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አትሌት ደጀኔ መገርሳ በ2:05:59 ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል ።
በስፔን ሲቪያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ቀንቷቸዋል።
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገው የማራቶን ውድድር አሸንፏል ።
አትሌት ሰለሞን 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ14 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት ማሸነፍ ችሏል ።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዲሱ ተስፋሁን 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ27 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በሴቶቹ ምድብ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ17 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ አሸንፋለች።
አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ አምስተኛ ሆና አጠናቃለች ።




