ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
#####################################################
ጥር 09/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየሰጠ ይገኛል ።
ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት አንዱ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ይገኛል ።
ስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።





