የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ ።
የካቲት 12/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሁለተኛ ዙር የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአሰልጣኞች ስልጠና በሣይንሳዊ መንገድ ወቅቱን የዋጀ ዘርፈ ብዙ ስልጠና በንደፈ ሃሳብና በተግባር ከየካቲት 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት ጀምረዋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማህበር ጋር በመተባበር ስልጠናው ለ24 ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የማሰልጠኛ ማዕከላት ባለሙያዎች በኢትዮጵያውያን ኢንስትራክተሮች አድማሱ ሳጂ እና ሳሙኤል ብርሃኑ እየተሰጠ ይገኛል ።
የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ላይ ከሚሳተፉት ሰልጣኞች መካከል 60% ሴቶች ናቸው።
በአንደኛው ዙር የዓለም አትሌቲክስ አንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ለ24 ሰልጣኞች መሰጠቱ የሚታወስ ነው።
ስልጠናው እስከ የካቲት 24/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል የወጣው መርሀግብር ያመላክታል ።




