ዛሬ በተከናወኑ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
***************************************************************************
የካቲት 09/2017 ዓ.ም
ዛሬ የካቲት 09/2017 ዓ.ም በተከናወኑ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅቷል ።
በስፔን ፋክሰ ካስቴዮ የ10 ኪሎሜትር ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል ።
በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ሲያሸንፉ አትሌት መዲና ኢሳ 29 ደቂቃ ከ25 ሴኮንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ ስታሸንፍ ፣ አትሌት ልቅና አንባው ሁለተኛ ፤ አትሌት ዓይንአዲስ መብራቱ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶቹ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ 26ደቂቃ ከ31ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቱ እና የቦታው አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸንፏል።
አትሌት ኩማ ግርማ ሁለተኛ አትሌት እንዲሁም አትሌት መልክነህ አዘዘ ስድስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በኦርሌን የ1500 ሜትር የሴቶች የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትሎ በመግባት አሸንፏል ።
በፓላንድ በተካሄደው ኦርሌን ኮፐርኒከስ ካፕ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 3:53.92 የወሰደባት ሲሆን የቦታው ፈጣን ሰዓት እና ሁለተኛው የዕርቀቱ ፈጣን ሰዓት ነው ።
አትሌት ብርቄ ሃይሎም 3:59.82 በመግባት ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በ4:02.19 ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች 1500 ሜትር ውድድር አትሌት ቢኒያም መሐሪ በ3:35.70 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል ።
በተመሳሳይ በኦርሌን ሴቶች 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፏል ።
የሴቶች 800 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ አሸንፋለች ።
አትሌት ፅጌ 2:00.04 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች ።
አትሌት ሀብታም አለም በበኩሏ በ2:00.61 በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።




