የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ ገለፀ ።
###########################################################
ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው ምርጫ ላይ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አድርጎ በመምረጡ የተሰማውን ደስታ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢሮ በመገኘት የእቅፍ አበባና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሞዴል አውሮፕላን በማስታወሻነት በማበርከት ደስታቸውን ገልፀውላቸዋል ።
ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገራችን ኩራት መሆኑን ካነሱ ብኃላ ፌዴሬሽኑ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ በመሆን ኢትዮጵያን ማስጠራታቸው አንስተዋል ።
ፕሬዚዳንቱ አክሎም አየር መንገዱ የአትሌቲክሱ የጀርባ አጥንት መሆኑን በማንሳት ቀጣይም በርካታ ስራ መስራት እንደሚገባና በአለምአቀፍ ደረጃ አገራችንን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።



See insights and ads