ዛሬ በተከናወኑ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀናጅተዋል።
###################################################
ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ እና አትሌት ሩቲ አጋ በ2025 የዢያሜን የማራቶን ውድድር አሸንፈዋል፡፡
በሺያመን ማራቶን 2025 የወንዶች ውድድር
አትሌት ዳዊት ወልዴ 2:06:06 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፏል፡፡
አትሌት አሰፋ ቦኪ ውድድሩን በ2፡06፡32 በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ ውድድሩን 2፡18፡46 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፋለች ።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ በቻይና ሆንግ ኮንግዙሃይማካው ድልድይ በተካሄደው የወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር 1፡1፡27 በመግባት አሸናፊ ሆኗል።
በሌላ ዜና በስፔን ኢልጋቡር በተደረገ የአገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፏል ።
በወንዶች የ10 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ 29 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል ።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በ29 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል ።
በሴቶች 5 ኪሎሜትር አትሌት መልክናት ውዱ በ26ደቂቃ 31 ሰከንድ 2ኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች ።





See insights and ads