የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን
በአዲስአበባ እና አቃቂ ቃሊቲ ስቴዲየም !
#############################
የካቲት 4/2018 ዓ.ም
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ ስቴዲየም እና ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የአቃቂ ቃሊቲ ስቴድየም ጎብኝተዋል።
ዳይሬክተሩ ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ መኪዩ መሀመድ እና ከፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ኢትዮጵያ በቀጣይ ለማስተናገድ ከታቀደው ዓለምአቀፍ ውድድር ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርጓል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባደረገላቸው ግብዣ መሠረት ትናንት አዲስአበባ የገቡት ዳይሬክተሩ፣ዛሬ ባደረጉት ጉብኝት ላይ የተሰሩቱን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች ካደነቁ ብኃላ፣”ኢትዮጵያ በቂ የትራንስፖርት ፣ሆቴል አገልግሎት እና ስታዲዮሞች ስላሏት ዓለምአቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ ትችላለች ብሏል።
ትናንት ዳይሬክተሩ፣
በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው
የአደይአበባ ዓለምአቀፍ የመለማመጃ ትራክ እና በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስቴዲየም መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።













