“ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን “:-የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን

#############################

የካቲት 4/2018 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በጋራ በመሆን ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ በርካታ ጀግኖች ስመጥር አትሌቶች ያፈራች አገር ናት፣ በአለም አትሌቲክስ ትልቅ ስምና ዝና ያላት መሆኗ አንስተው፣ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው እና በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እንደተደሰቱ ገልጿል ።

ዳይሬክተሩ አክሎም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን ለማዘጋጀት በቂ አቅም እንዳላትና፣የተለያዩ ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ እናስመጣለን ብሏል።

ዳይሬክተሩ በተጨማሪም በመገባደድ ላይ የሚገኘው አደይአበባ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም፣ አዲስአበባ እና አቃቂ ቃሊቲ ጨምሮ የተለያዩ በመገንባት ላይ የሚገኙትን እንዲጠናቀቁ እና ውድድሮችን ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ጠይቀዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጣም ጠንካራ ተቋም እንደሆነ እና ከዓለም አትሌቲክስ የጀመረውን መልካም ግንኙነት እንዲቀጥል ያሳሰቡ ሲሆን፣በቅርብ የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተናግሯል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ አንስተው አሁን የተጀመረው የስፖርት ዲፕሎማሲ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል ።

ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት የሚያስችል ሙሉ ቁመና ላይ እንገኛለን ያሉ ሲሆን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን በመዘርጋት እንደሚሰሩና፣ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ተወካይ እንዲኖራት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል ።

ፕሬዝዳንቱ በመጨረሻም የተጀመሩት በርካታ አመርቂ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች መንግስት ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ አመስግነው ፣ውድድሮችን ለማስተናገድ እንዲያስችሉ የቀሩትን ስራዎች እንዲጠናቀቁ፣ መንግስት እንዲያግዛቸው ጥሪ አቅርቧል ።

በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ከፌዴሬሽኑ የባህል ልብስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

Categories: Uncategorized