ክብርት ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለአንጋፋ አትሌቶች ድጋፍ አደረጉ ።

::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

የካቲት 22/2018ዓ.ም

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ዓለምአቀፍ እና አህጉርአቀፍ ውድድሮች የኢትዮጵያን ስም ያስጠሩ አንጋፋ አትሌቶች ድጋፍ አደረጉ።

ለቀድሞ አትሌት ኮማንደር ጌጤ ኡርጌ የቤት እና 10 ሚሊየን ብር ከነሙሉ የቤት እቃ በክብርት ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አስተባባሪነት ከባለሃብቶች በተሰበሰበ ብር ድጋፍ ተደርጓል ።

በዛሬው እለትም ክብርት ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች በአትሌቷ ቤት በመገኘት የአትሌቷን ቤት በመመረቅ ለአንጋፋዋ አትሌት ጌጤ ኡርጌ ከህመሟ እስክትድን ድረስ ሙሉ የህክምና ወጪዋን እንደሚሸፍኑ ቃል በመግባት

ለ10 አንጋፋ አትሌቶች ለእያንዳዳቸው የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በቀጣይም ከፌዴሬሽኑ ጋር በመሆን ለሌሎች አንጋፋ አትሌቶችን ለመደገፍ አበክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ።

ኮማንደር አትሌት ስለሽ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

ለተረሱ ፣ለተቸገሩ አንጋፋ አትሌቶች ላደረጉት ትልቅ ድጋፍ አመስግነዋል ።

ፕሬዝዳንቱ አክሎም

ከአንጋፋ አትሌቶች ጋር በመሆን ሌሎችን የተቸገሩ አንጋፋ አትሌቶችን ለማገዝ እንደሚሰሩ አንስተዋል ።

በአለም አትሌቲክስ ፣በአፍሪካ አትሌቲክስ ውድድሮች ሀገራቸውን የወከሉ የአገራቸውን ስም ያስጠሩ በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ችግር ውስጥ ያሉ

የሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ የተደረገላቸው አንጋፋ አትሌቶች ስም ዝርዝር :-

1.አትሌት ሸዋንግዛው ወርቁ 2,000,000 ብር

2.አትሌት አጥሬ በዛብህ። 2,000,000 ብር

3.አትሌት ወርቁ ባሮ 2,000,000 ብር

4 .አትሌት ዋሚ ቢራቱ 2,000,000 ብር

5.አትሌት ዘውዴ ሃይለማርያም 2,000,000 ብር

6.አትሌት ግርማ ወልደሃና 2,000,000 ብር

7 .አትሌት ሸይቱ ሽፈራው 2,000,000 ብር

8.አትሌት ወልዴ ሮበሌ 2,000,000 ብር

9 .አትሌት ጌታቸው ከበደ 2,000,000 ብር

አትሌት ሸምሱ ሀሰን 2,000,000 ብር

10. አትሌት ሸምሱ ሀሰን 2,000,000 ብር

Categories: Uncategorized